ኢዮአብም፥ “አንተ በዚች ቀን የምሥራች የምትናገር ሰው አይደለህም፤ ወሬውን በሌላ ቀን ትናገራለህ፤ በዚች ቀን ግን የንጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አትናገርም” አለው።
2 ሳሙኤል 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየኸውንም ሁሉ ለንጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢዮአብ ሰግዶ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፣ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው፤ ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፥ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው። ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ኵሲን፦ ሂድ ያየኸውንም ለንጉሡ ንገር አለው። ኵሲም ለኢዮአብ እጅ ነሥቶ ሮጠ። |
ኢዮአብም፥ “አንተ በዚች ቀን የምሥራች የምትናገር ሰው አይደለህም፤ ወሬውን በሌላ ቀን ትናገራለህ፤ በዚች ቀን ግን የንጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አትናገርም” አለው።
ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ኢዮአብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከትዬ፥ እባክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮአብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮጣለህ? ተመለስ፤ ብትሄድ ይች ወሬ ለጥቅም አትሆንህምና” አለ።
እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው።
እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።