2 ሳሙኤል 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ኢዮአብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከትዬ፥ እባክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮአብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮጣለህ? ተመለስ፤ ብትሄድ ይች ወሬ ለጥቅም አትሆንህምና” አለ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ኢዮአብን፦ የሆነ ሆኖ ኵሲን ተከትዬ፥ እባክህ፥ ልሩጥ አለው። ኢዮአብም፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም ወሬ የምትወስድ አይደለህምና ትሮጥ ዘንድ ለምን ትወድዳለህ? አለ። Ver Capítulo |