ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
2 ሳሙኤል 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥሩም የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ከበቡት፤ አቤሴሎምንም መትተው ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ዐሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ዐሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ የኢዮአብ አጃቢዎች ከሆኑ ወታደሮች ዐሥሩ ወደ አቤሴሎም ሄደው ዙሪያውን በመክበብ በጦር መሣሪያ ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥሩም የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ከበቡት፥ አቤሴሎምንም መትተው ገደሉት። |
ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
ኢዮአብም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው።
ንጉሡ ዳዊትም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ አላቸው፥ “ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦ የእስራኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶአልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለምን ዘገያችሁ?