እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
2 ሳሙኤል 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በሰውነቱ ላይ ክፉ ነገር ባደርግ ነገሩ በንጉሡ ዘንድ ባልተሰወረም ነበር፤ አንተም በተነሣህብኝ ነበር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቈርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፣ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለሌለ፣ አንተም ራስህ አትቀርበኝም ነበር” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቆርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፥ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለ ሌለ፥ አንተም ራስህ በተነሣህብኝ ነበር” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ እኔ የንጉሡን ትእዛዝ በመጣስ አቤሴሎምን ገድዬ ቢሆን ኖሮ፥ ንጉሡ ሁሉን ነገር እንደሚሰማ ይህንንም መስማቱ አይቀርም፤ አንተም እኔን ለማዳን አትከላከልልኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ቅሉ በነፍሱ ላይ ብወነጅል ኖሮ ይህ ከንጉሥ ባልተሰወረም፥ አንተም በተነሣህብኝ ነበር አለው። |
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።