2 ሳሙኤል 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሲም አቤሴሎምን አለው፥ “አኪጦፌል በዚህ ጊዜ የመከራት ምክር መልካም አይደለችም። ይችውም አንዲት ናት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ የሚያዋጣ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ መልካም አይደለም፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በአሁኑ ሰዓት አኪጦፌል የሰጣችሁ ምክር ጥሩ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም አቤሴሎምን፦ አኪጦፌል በዚህ ጊዜ የመከራት ምክር መልካም አይደለችም አለው። |
ወደ ከተማ ግን ተመልሰህ ለአቤሴሎም፦ ወንድሞችህ፥ ንጉሡም መጡ። እነሆ፥ በኋላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገልጋይህ ነኝ፤ አስቀድሞ ለአባትህ አገልጋይ ነበርሁ፥ እንዲሁ አሁንም ለአንተ አገልጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብትለው የአኪጦፌልን ምክር ትለውጥልኛለህ።
አኪጦፌልም አቤሴሎምን፥ “ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፤ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈርኸው ይሰማሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል” አለው።
ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን” ብሎ ተናገረው።