2 ሳሙኤል 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም፥ “አርካዊውን ኩሲን ጥሩት፤ ደግሞም እርሱ የሚለውን እንስማ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎም ግን፣ “እስኪ ደግሞ አርካዊውን ኩሲን ጥሩትና የሚለውን እንስማ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሴሎም፥ “እስቲ ደግሞ አርካዊውን ሑሻይን ጥሩትና የሚለውን እንስማ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎምም “አሁን ደግሞ አርካዊውን ሑሻይን ጥሩትና እርሱ የሚለውን እንስማ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም፦ አርካዊውን ኩሲን ጥሩ፥ ደግሞም እርሱ የሚለውን እንስማ አለ። |
ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን” ብሎ ተናገረው።
እርሱም፥ “አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” አላቸው።