ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብሱን ቀደደ፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።
2 ሳሙኤል 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ወዳጅ ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ አቤሴሎምን፥ “ንጉሥ ሆይ! ሽህ ዓመት ያንግሥህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ሑሻይም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ወዳጅ አርካዊው ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ፦ ሺህ ዓመት ያንግሥህ አለው። |
ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብሱን ቀደደ፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።
ወደ ከተማ ግን ተመልሰህ ለአቤሴሎም፦ ወንድሞችህ፥ ንጉሡም መጡ። እነሆ፥ በኋላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገልጋይህ ነኝ፤ አስቀድሞ ለአባትህ አገልጋይ ነበርሁ፥ እንዲሁ አሁንም ለአንተ አገልጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብትለው የአኪጦፌልን ምክር ትለውጥልኛለህ።
እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱን አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ ይላሉ።
በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ቀብተው ያንግሡት፤ መለከትም ነፍታችሁ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ በሉ።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ፥ “ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደ ሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን?” አላቸው፤ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እልልታ አደረጉ።