ቃየልም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።
2 ሳሙኤል 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኔም ለአገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ በሜዳም ተጣሉ፤ የሚገላግላቸውም አልነበረም፤ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፣ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፥ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእኔም ለባሪያህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፥ በሜዳም ተጣሉ፥ የሚገላግላቸውም አልነበረም፥ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው። |
ቃየልም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።
የአቤሴሎምም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ።
እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
በሁለተኛውም ቀን ወጣ፤ ሁለቱም የዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፤ ሙሴም በዳዩን፥ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።