La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችና አን​ዲት ሴት ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የሴ​ቲቱ ልጅም ስም ትዕ​ማር ይባ​ላል። ያች​ውም ሴት መልከ መል​ካም ነበ​ረች፤ እር​ሷም የሰ​ሎ​ሞን ልጅ የሮ​ብ​አም ሚስት ሆና አቢ​ያን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የተባለች አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፤ ሴት ልጁም በጣም ውብ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የተባለች አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፤ ሴት ልጁም በጣም ውብ ነበረች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ነበሩት፤ የሴት ልጁም ስም ትዕማር ሲሆን እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፥ የሴቲቱም ልጅ ስም ትዕማር ነበረ፥ እርስዋም የተዋበች ሴት ነበረች።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 14:27
6 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ለዳ​ዊት ልጅ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም አን​ዲት የተ​ዋ​በች እኅት ነበ​ረ​ችው፤ ስም​ዋም ትዕ​ማር ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጅ አም​ኖን ወደ​ዳት።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታ​ሰ​ቢያ የሚ​ሆን ልጅ የለ​ኝም” ብሎ ሐው​ልት ወስዶ በን​ጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐው​ልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤ​ሴ​ሎም” ተብላ ትጠ​ራ​ለች።


“በእ​ነ​ርሱ ላይ እነ​ሣ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ስም​ንና ቅሬ​ታን፥ ዘር​ንና ትው​ል​ድ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።