La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​ና​ዳ​ብም አለው፦“ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብለህ በአ​ል​ጋህ ላይ ተኛ፤ አባ​ት​ህም ሊያ​ይህ ይመ​ጣል፦ እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ የም​በ​ላ​ውን እን​ጀራ እን​ድ​ት​ሰ​ጠኝ፥ መብ​ሉ​ንም እኔ እያ​የሁ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በ​ላው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ በለው።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮናዳብም፣ “እንግዲያው ‘ታምሜአለሁ’ ብለህ ዐልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፣ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ብትሰጠኝ ደስ ይለኛል፤ መብሉንም እዚሁ አጠገቤ ሆና እያየሁ አዘጋጅታ በእጇ እንድታጐርሰኝ እባክህ ፍቀድልኝ ብለህ ንገረው፣’ ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናዳብም፥ “እንግዲያው የታመምህ መስለህ አልጋ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፥ ‘እኅቴ ትዕማር መጥታ የምበላውን ነገር ትስጠኝ፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርሷ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናዳብም እንዲህ አለው፤ “ይህ ከሆነ እንግዲህ የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣ፥ ‘እኅቴ ትዕማርን መጥታ እንድታስታምመኝ እባክህ ንገራት፤ እዚህ በአጠገቤ እያየኋት ምግብ አዘጋጅታ እርስዋ ራስዋ እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ’ በለው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮናዳብም፦ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፥ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 13:5
8 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም፥ “የን​ጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ​ምን በየ​ቀኑ እን​ዲህ ከሳህ? አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን?” አለው። አም​ኖ​ንም፥ “የወ​ን​ድ​ሜን የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን እኅት ትዕ​ማ​ርን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ” አለው።


እን​ዲ​ሁም አም​ኖን፥ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉ​ሡም ሊያ​የው መጣ፤ አም​ኖ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ እያ​የሁ ሁለት እን​ጎቻ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በላ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


አኪ​ጦ​ፌ​ልም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ቤት ሊጠ​ብቁ ወደ ተዋ​ቸው ወደ አባ​ትህ ቁባ​ቶች ግባ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ት​ህን እን​ዳ​ሳ​ፈ​ር​ኸው ይሰ​ማሉ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃ​ቸው ይበ​ረ​ታል” አለው።


የአባቱን ትምህርት ከመጠበቅ የሚከለከል ልጅ፥ ክፉ ቃልን ይማራል።


አሁ​ንም እና​ንተ ከሸ​ን​ጎው ጋር ወደ ሻለ​ቃው ሂዱና የም​ት​መ​ረ​ም​ሩ​ትና የም​ት​ጠ​ይ​ቁት አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጣው ንገ​ሩት፤ እኛ ግን ወደ እና​ንተ ከመ​ድ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ገ​ድ​ለው ቈር​ጠ​ናል።”