ባቱኤልና ላባም መለሱ፤ እንዲህም አሉ፥ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል፤ ክፉ ወይም በጎ ልንመልስልህ አንችልም።
2 ሳሙኤል 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካም አልተናገረውም። እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት አቤሴሎም አምኖንን ጠልቶታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም፤ ምክንያቱም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎም ግን አምኖን እኅቱን ትዕማርን ስለደፈራት፥ ከጥላቻው የተነሣ አምኖንን ክፉም ሆነ ደግ አንዳች ቃል አልተናገረውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና በመድፈሩም ምክንያት አቤሴሎም አምኖንን እጅግ ጠላው፤ ዳግመኛም ክፉም ሆነ ደግ ሊያነጋግረው አልፈለገም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም እኅቱን ትዕማርን ስላሳፈራት አምኖንን ጠልቶታልና አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካምም አልተናገረውም። |
ባቱኤልና ላባም መለሱ፤ እንዲህም አሉ፥ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል፤ ክፉ ወይም በጎ ልንመልስልህ አንችልም።
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።
ንጉሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበኵር ልጁ ነበረና ስለ ወደደው የልጁን የአምኖንን ነፍስ አላሳዘነም።
ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።