La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ነው​ሬን ወዴት እጥ​ላ​ታ​ለሁ? አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሰ​ነ​ፎች እንደ አንዱ ትሆ​ና​ለህ፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ለን​ጉሡ ንገ​ረው፥ እኔ​ንም አይ​ነ​ሣ​ህም” አለ​ችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተስ ብትሆን በእስራኤል ሞኞች እንደ አንዱ መቈጠርህ አይደለምን? እባክህ ለንጉሡ ንገረው፤ እንዳላገባህም አይከለክለኝም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል ከወራዳዎቹ እንደ አንዱ ትቆጠራለህ፤ እባክህ ለንጉሡ ጠይቀው፤ እኔንም አይከለክልህም።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደዚህ ካዋረድከኝ በኋላ በሕዝብ ፊት ራሴን ቀና አድርጌ ለመሄድ እንዴት እችላለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል እጅግ የተዋረድክ ትሆናለህ፤ ይልቅስ ለንጉሡ ብትነግረው እኔን ለአንተ በሚስትነት እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ነኝ” አለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከምናምንቴዎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፥ እንግዲህስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም አለችው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 13:13
4 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ወን​ድን ያላ​ወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነ​ር​ሱን ላው​ጣ​ላ​ችሁ፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁም አድ​ር​ጉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታ​ድ​ርጉ፤ እነ​ርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብ​ተ​ዋ​ልና።”


እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።


ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ድን​ግል ልጄና የእ​ር​ሱም ዕቅ​ብት እነሆ፥ አሉ፤ አሁ​ንም አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አዋ​ር​ዱ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም ፊት ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እን​ደ​ዚህ ያለ የስ​ን​ፍና ሥራ አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው።