La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች፥ “ሕፃኑ በሕ​ይ​ወት ሳለ ብን​ነ​ግ​ረው አል​ሰ​ማ​ንም፤ ይል​ቁ​ንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብን​ነ​ግ​ረው እን​ዴት ይሆን? በራሱ ላይ ክፉ ያደ​ር​ጋል” ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፣ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም፤ ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጕዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፥ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከአንድ ሳምንትም በኋላ ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት ባለሟሎችም መርዶውን ለመንገር ፈርተው “ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ እንኳ ዳዊት ስንመክረው አልሰማንም፤ ታዲያ፥ አሁን የልጁን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? ምናልባት በራሱ ላይ አንዳች ጒዳት ማድረስ ይችል ይሆናል!” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳዊትም ባሪያዎች፦ ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፥ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን? በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 12:18
3 Referencias Cruzadas  

የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።


ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖቹ በሹ​ክ​ሹ​ክታ ሲነ​ጋ​ገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሕፃኑ ሞቶ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሞቶ​አል” አሉት።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።