Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 12:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖቹ በሹ​ክ​ሹ​ክታ ሲነ​ጋ​ገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሕፃኑ ሞቶ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሞቶ​አል” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፣ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፣ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፥ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፥ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ዳዊት እርስ በርሳቸው ሲያንሾካሹኩ በሰማ ጊዜ ሕፃኑ መሞቱን ተረዳ፤ ስለዚህም “ሕፃኑ ሞተ እንዴ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “አዎ ሞቶአል” ሲሉ መለሱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ዳዊትም ባሪያዎቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ አወቀ፥ ዳዊትም ባሪያዎቹን፦ ሕፃኑ ሞቶአል? አላቸው። እነርሱም፦ ሞቶአል አሉት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 12:19
4 Referencias Cruzadas  

በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች፥ “ሕፃኑ በሕ​ይ​ወት ሳለ ብን​ነ​ግ​ረው አል​ሰ​ማ​ንም፤ ይል​ቁ​ንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብን​ነ​ግ​ረው እን​ዴት ይሆን? በራሱ ላይ ክፉ ያደ​ር​ጋል” ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈሩ።


ዳዊ​ትም ከም​ድር ተነ​ሥቶ ታጠበ፤ ተቀ​ባም፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጠ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እን​ጀ​ራም አም​ጡ​ልኝ አለ፤ በፊ​ቱም እን​ጀራ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ በላም።


ንጉ​ሡም ዳዊት አቤ​ሴ​ሎ​ምን መከ​ታ​ተ​ልን ተወ፤ ስለ ሞተው ልጁ ስለ አም​ኖን ተጽ​ና​ንቶ ነበ​ርና።


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ!ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos