የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳዊትም አገልጋዮች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፤ ኬጤያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
2 ሳሙኤል 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም የጦርነቱን ዜና ሁሉ ለዳዊት ይነግሩት ዘንድ ላከ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ስለ ጦርነቱ የሚያስረዳ መልእክት ወደ ዳዊት ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ልኮ በሰልፍ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት ነገረው። |
የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳዊትም አገልጋዮች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፤ ኬጤያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።
መልእክተኛም መጥቶ፥ “የንጉሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥተዋል” ብሎ ነገረው። ንጉሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው” አለ።