La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለዳ​ዊ​ትም ስለ ሰዎቹ ነገ​ሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍ​ረው ነበ​ሩና ተቀ​ባ​ዮ​ችን ላከ። ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪኮ ቈዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፥ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪ፥ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አፈሩ፤ ዳዊት ስለ ሆነው ነገር በሰማ ጊዜ መልእክተኞች ልኮ በኢያሪኮ እንዲቈዩና ጺማቸውም እንደገና እስከሚያድግ እንዳይመለሱ ነገራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ያን በሰማ ጊዜ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበሩና ተቀባዮች ላከ። ንጉሡም፦ ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ አላቸው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 10:5
6 Referencias Cruzadas  

ሐኖ​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ገሚስ ላጨ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ከሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


በእ​ር​ሱም ዘመን የቤ​ቴል ሰው አኪ​ያል ኢያ​ሪ​ኮን ሠራ፤ በነ​ዌም ልጅ በኢ​ያሱ ቃል እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ በበ​ኵር ልጁ በአ​ቢ​ሮን መሠ​ረ​ቷን አደ​ረገ፥ በታ​ናሹ ልጁም በዜ​ጉብ በሮ​ች​ዋን አቆመ።


ሰዎ​ችም ሄደው በሰ​ዎቹ ላይ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለዳ​ዊት አስ​ታ​ወ​ቁት። ሰዎ​ቹም በብዙ አፍ​ረ​ዋ​ልና ይቀ​በ​ሏ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን ላኩ፤ ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፥ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አለ።


ኢያ​ሪ​ኮም በግ​ንብ ታጥራ ተዘ​ግታ ነበር፤ ወደ እር​ስዋ የሚ​ገባ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ወጣ አል​ነ​በ​ረም።