2 ሳሙኤል 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውንም ሕዝብ ከወንድሙ ከአቢሳ ጋር ላከ፤ በአሞን ልጆች ፊትም አሰለፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ግንባር አሰለፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ግንባር አሰለፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠራዊቱ ቀሪውን ክፍል በወንድሙ በአቢሳይ ትእዛዝ ሥር አደረገ፤ አቢሳይም እነርሱን በዐሞናውያን ፊት ለፊት አሰለፋቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውንም ሕዝብ በወንድሙ በአቢሳ እጅ አድርጎ በአሞን ልጆች ፊት ለሰልፍ አኖራቸው። |
ኢዮአብም በፊትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ጐልማሶችን ሁሉ መረጠ፤ በሶርያውያንም ፊት አሰለፋቸው።
ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው።
የሶርህያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበር። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ ስሙም በሦስቱ ዘንድ ተጠርቶ ነበር።