2 ሳሙኤል 1:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃዎች እንዴት ጠፉ!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኀያላን እንዴት ወደቁ? የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃ እንዴት ጠፋ! |
ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላቸውና ፈረሰኛቸው” አለ።
ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእስራኤል ኀይላቸውና ጽንዓቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ ዳግመኛ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ቀደደው።