ስለዚህ እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፤ ድርሻሽንም አጕድያለሁ፤ ለሚጠሉሽም፥ ከመንገድሽ ለመለሱሽና ለአሳቱሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
2 ሳሙኤል 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን በጋት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁት፤ የፍልስጥኤም ቈነጃጅት አይደሰቱ፤ ያልተገረዙት ሴቶች ልጆች እልል አይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍልስጥኤም ቆነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፤ ያልተገረዙት ሴት ልጆች እልል እንዳይሉ፤ ይህን በጌት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፥ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ ይህን ወሬ በጋት አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ አታውጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍልስጥኤማውያን ቈነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፥ የቆላፋንም ቈነጃጅት እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፥ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ። |
ስለዚህ እነሆ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቻለሁ፤ ድርሻሽንም አጕድያለሁ፤ ለሚጠሉሽም፥ ከመንገድሽ ለመለሱሽና ለአሳቱሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ።
ክፋትሽ እንደ ዛሬው ሳይገለጥ ለሶርያ ሴቶች ልጆችና ለጐረቤቶችዋ ሁሉ በዙሪያሽም ለሚከቡሽ ፍልስጥኤማውያት ሴቶች ልጆች መሰደቢያ ሆነሻል።
ዮፍታሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትቀበለው ወጣች፤ ለእርሱም የሚወድዳት አንዲት ብቻ ነበረች። ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው።
ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደረግለታል? የሕያው አምላክን ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ብሎ ተናገራቸው።
እኔ ባሪያህ አንበሳና ድብ ገደልሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል። እንግዲህ እገድለው ዘንድ፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን አስወግድ ዘንድ ዛሬ አልሄድምን? የሕያው አምላክ ጭፍሮችን ይገዳደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምንድን ነው?”
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ፥ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ዳዊትን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ “እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይወጉኝና እንዳይሳለቁብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለ። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።
ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን።