2 ሳሙኤል 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከወደቀ በኋላ አለመዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱም ላይ የነበረውን ዘውድ፥ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፤ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መቼም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፣ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፤ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፥ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና በክንዱ ላይ የነበረውን አንባር ወስጄ፥ እነሆ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ከወደቀ በኋላ አለ መዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፥ በራሱም ላይ የነበረውን ዘውድ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፥ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት። |
የንጉሣቸውንም የሜልኮምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕንቍም ነበረበት፤ ዳዊትም በራሱ ላይ አደረገው። ከከተማዪቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።
እርሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግሬውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደለችው እንዳይሉ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፤ ጐልማሳውም ወጋው፤ አቤሜሌክም ሞተ።
ንጉሡም ዶይቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህናቱን ግደላቸው” አለው። ሶርያዊው ዶይቅም ዞሮ ካህናቱን ገደላቸው፤ በዚያም ቀን የበፍታ ኤፉድ የለበሱትን ሦስት መቶ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ።