2 ጴጥሮስ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን መላእክት በኀይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ፥ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መላእክት ከእነርሱ ይልቅ ብርቱና ኀያል ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብ ቃል አይሰነዝሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን መላእክት፥ በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ምንም ያህል ቢልቁ፥ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላእክት ከእነርሱ በኀይልና በሥልጣን የሚበልጡ ቢሆኑም እንኳ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋን የተመላ ክስ አያቀርቡባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም። |
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።