የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።
2 ነገሥት 8:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአክዓብም ቤት መንገድ ሄደ፤ እንደ አክዓብም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝያስ ከአክዓብ ቤተ ሰብ ጋራ በጋብቻ የተሳሰረ ስለ ነበር፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝያስ የንጉሥ አክዓብ ዐማች ከመሆኑ የተነሣ ልክ እንደ አክዓብ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝያስ የንጉሥ አክዓብ ዐማች ከመሆኑ የተነሣ ልክ እንደ አክዓብ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአክዓብም ቤት መንገድ ሄደ፤ እንደ አክዓብም ቤት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ለአክዓብ ቤት አማች ነበረና። |
የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።