2 ነገሥት 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአገልጋዮችህ ጋር ለመሄድ ና” አለ። ኤልሳዕም፥ “እሽ እኔም እመጣለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመካከላቸውም አንዱ፣ “አንተስ ከአገልጋዮችህ ጋራ አትመጣምን?” አለው። ኤልሳዕም፣ “ዕሺ እመጣለሁ” አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነቢያቱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም በጥያቄው ተስማማ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነቢያቱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም በጥያቄው ተስማማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም አንዱ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከባሪያዎችህ ጋር ለመሄድ ፍቀድ፤” አለ። እርሱም “እሄዳለሁ” አለ። |
ንዕማንም፥ “ሁለት የብር መክሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለቱንም መክሊት ብር ተቀብሎ በሁለት ከረጢት ውስጥ ጨመረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ።
ወደ ዮርዳኖስም እንሂድ፤ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የምናድርበትም ቤት እንሥራ፥” አሉት፤ እርሱም፥ “ሂዱ” አለ።
ሁለቱም በአንድ ላይ ተቀመጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብላቴናዪቱም አባት ሰውዬውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብህንም ደስ ይበለው” አለው።
ባርቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብትሄጂ እኔ እሄዳለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባትሄጂ እኔ አልሄድም፤ እግዚአብሔር መልአኩን ከእኔ ጋር የሚልክበትን ዕለት አላውቃትምና” አላት።