ቀትርም በሆነ ጊዜ ወጡ፤ ወልደ አዴርም በማቅ ድንኳን ውስጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበረ፤ የሚረዱት ሠላሳ ሁለት ነገሥታትም አብረውት ነበሩ።
2 ነገሥት 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ስውር ቦታም በደረሱ ጊዜ ከእጃቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖራቸው፤ ሰዎቹንም አሰናበተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግያዝም ወደ ኰረብታው እንደ ደረሰ፣ ዕቃዎቹን ከአገልጋዮቹ ተቀብሎ በቤቱ ውስጥ አስቀመጠ፤ ሰዎቹንም አሰናብቷቸው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕ ወደሚኖርባትም ኰረብታ በደረሱ ጊዜ፥ ግያዝ ሁለቱን ከረጢት ተቀብሎ ወደ ቤት አስገባ፤ ከዚያም በኋላ የንዕማንን አገልጋዮች አሰናብቶአቸው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕ ወደሚኖርባትም ኰረብታ በደረሱ ጊዜ፥ ግያዝ ሁለቱን ከረጢት ተቀብሎ ወደ ቤት አስገባ፤ ከዚያም በኋላ የንዕማንን አገልጋዮች አሰናብቶአቸው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኮረብታውም በመጣ ጊዜ ከእጃቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖራቸው፤ ሰዎቹንም አሰናበተ፤ እነርሱም ሄዱ። |
ቀትርም በሆነ ጊዜ ወጡ፤ ወልደ አዴርም በማቅ ድንኳን ውስጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበረ፤ የሚረዱት ሠላሳ ሁለት ነገሥታትም አብረውት ነበሩ።
ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ወዮላቸው! ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፥ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!
እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።
በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፤ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።