La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የደ​ማ​ስቆ ወን​ዞች ባብ​ናና ፋርፋ ከእ​ስ​ራ​ኤል ውኆች ሁሉ አይ​ሻ​ሉ​ምን? ሄጄስ በእ​ነ​ርሱ ውስጥ መጠ​መ​ቅና መን​ጻት አይ​ቻ​ለ​ኝም ኖሮ​አ​ልን?” ብሎ በቍጣ ተመ​ልሶ ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለዚህ ለዚህ የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋር ከየትኞቹም የእስራኤል ውሆች አይሻሉምን? ለመታጠብ ለመታጠብማ በእነርሱ ታጥቤ መንጻት አልችልምን?” ስለዚህ በቍጣ ተመለሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የውሃ የውሃማ በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋር አይሻሉምን? እንዲህ ከሆነማ በእነርሱ ታጥቤ በነጻሑ ነበር!”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የውሃ የውሃማ በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋር አይሻሉምን? እንዲህ ከሆነማ በእነርሱ ታጥቤ በነጻሑ ነበር!”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውሆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 5:12
14 Referencias Cruzadas  

በራሱ ላይ ያረ​ፈ​ች​ውን የኤ​ል​ያ​ስን መጠ​ም​ጠ​ሚያ ወስዶ ውኃ​ውን መታ​ባት፦ ውኃው ግን አል​ተ​ከ​ፈ​ለም፤ እር​ሱም፥ “የኤ​ል​ያስ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት ነው? እን​ዴ​ትስ ነው?” አለ። ከዚ​ህም በኋላ ውኃ​ውን በመታ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ኤል​ሳ​ዕም ተሻ​ገረ።


ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ወስዶ ጠቀ​ለ​ለው፤ የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ውኃ መታ​በት፤ ውኃ​ውም ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ሁለ​ቱም በደ​ረቅ ተሻ​ገሩ። ወጥ​ተ​ውም በም​ድረ በዳው ቆሙ።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


ንዕ​ማ​ንም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ወይም ሌላ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቀ​ር​ብ​ምና ሁለት የበ​ቅሎ ጭነት አፈር ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ይስ​ጡት።


ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።


ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።


ይቅር ባይ ሰው ይታገሣል፥ መመካቱም ኀጢአተኞችን ይቃወማቸዋል፥


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፣ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።


በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።