በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለበት፤ ወደ እግዚአብሔርም፥ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ እግዚአብሔርን ጠራው።
2 ነገሥት 4:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኖቹንም በዐይኖቹ፥ እጆቹንም በእጆቹ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ሰውነት ሞቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐልጋው ላይ ወጥቶም በልጁ ላይ ተጋደመና አፉን በአፉ፣ ዐይኑን በዐይኑ፣ እጁን በእጁ ላይ አደረገ። ሙሉ በሙሉ እንደተዘረጋበትም፣ የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ አፉን ከአፉ፥ ዐይኖቹን ከዐይኖቹ፥ እጆቹን ከእጆቹ ጋር ገጥሞ በልጁ ሬሳ ላይ ተጋደመ፤ ኤልሳዕም ተዘርግቶ እንደ ተጋደመበት የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ አፉን ከአፉ፥ ዐይኖቹን ከዐይኖቹ፥ እጆቹን ከእጆቹ ጋር ገጥሞ በልጁ ሬሳ ላይ ተጋደመ፤ ኤልሳዕም ተዘርግቶ እንደ ተጋደመበት የልጁ ሰውነት መሞቅ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዐይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ። |
በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለበት፤ ወደ እግዚአብሔርም፥ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ እግዚአብሔርን ጠራው።
የእስራኤልንም ንጉሥ አለው፥ “እጅህን በቀስቱ ላይ ጫን።” ዮአስም እጁን በቀስቱ ላይ ጫነ፤ ኤልሳዕም እጁን በንጉሡ እጅ ላይ ጫነ፦