2 ነገሥት 4:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕ ወደ ቤት ሲገባም ልጁ ሞቶ በዐልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም በደረሰ ጊዜ ብቻውን ወደ ክፍሉ ገብቶ፥ ልጁ ሞቶ በአልጋው ላይ መጋደሙን አየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም በደረሰ ጊዜ ብቻውን ወደ ክፍሉ ገብቶ፥ ልጁ ሞቶ በአልጋው ላይ መጋደሙን አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአልጋ ላይ ተጋድሞ ነበር። |
ግያዝም በፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ግያዝም ቀድሞአቸው ደረሰ፤ በትሩንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኖረው፤ ነገር ግን ድምፅ ወይም መስማት አልነበረም፤ እርሱንም ሊገናኘው ተመልሶ፥ “ሕፃኑ አልተነሣም” ብሎ ነገረው።