La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 4:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሕ​ፃ​ኑም እናት፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም! አል​ተ​ው​ህም” አለች፤ ኤል​ሳ​ዕም ተነ​ሥቶ ተከ​ተ​ላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የልጁ እናት ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፤ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው፤ ስለዚህ ተነሥቶ ተከተላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርሷን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን “በምተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!” አለችው፤ ስለዚህ እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሕፃኑም እናት “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! አልተውህም፤” አለች፤ ተነሥቶም ተከተላት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 4:30
8 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እር​ሱም፥ “ያዕ​ቆብ ነኝ” አለው።


ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ልኮ​ኛ​ልና በዚሁ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው። ወደ ቤቴ​ልም ደረሱ።


ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ኢያ​ሪኮ ልኮ​ኛ​ልና፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው።


ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ልኮ​ኛ​ልና እባ​ክህ፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው፤ ሁለ​ቱም ሄዱ።


ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ለመ​ሄድ ና” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እሽ እኔም እመ​ጣ​ለሁ” አለ።


እር​ስ​ዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጸ​ለይ በዚህ በፊ​ትህ ቆማ የነ​በ​ረች ሴት እኔ ነኝ።