እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ እሳትን ከኋላህ አነድዳለሁ፤ ዐጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ድረስ የአክዓብን ዘር አጠፋዋለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ ያሉትንም፥ የሌሉትንም እነቅላለሁ፤
2 ነገሥት 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እስራኤልም ሰፈር በመጡ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው ሞዓባውያንን መቱ፤ እነርሱም ከፊታቸው ሸሹ፤ ሞዓባውያንንም እየመቱ ወደ ሀገሩ ውስጥ ገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓባውያን ወደ እስራኤል ሰፈር ሲወጡም፣ እስራኤላውያን ተነሥተው ወጓቸው፤ ሞዓባውያንም ከፊታቸው ሸሹ። ከዚያም እስራኤላውያን ምድሪቱን ወርረው ሞዓባውያንን ፈጇቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እነርሱ ወደ ሰፈር በደረሱ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው አደጋ በመጣል ወደ ኋላ መለሱአቸው፤ እስራኤላውያን አገሪቱን ወረው ሞዓባውያንን ጨፈጨፉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እነርሱ ወደ ሰፈር በደረሱ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው አደጋ በመጣል ወደ ኋላ መለሱአቸው፤ እስራኤላውያን አገሪቱን ወረው ሞአባውያንን ጨፈጨፉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እስራኤል ሰፈር በመጡ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው ሞዓባውያንን መቱ፤ እነርሱም ከፊታቸው ሸሹ፤ ሞዓባውያንንም እየመቱ ወደ አገሩ ውስጥ ገቡ። |
እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ እሳትን ከኋላህ አነድዳለሁ፤ ዐጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ድረስ የአክዓብን ዘር አጠፋዋለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ ያሉትንም፥ የሌሉትንም እነቅላለሁ፤
“ይህ የጦር ደም ነው፤ እነዚያ ነገሥታት እርስ በርሳቸው ተጋደሉ፤ ባልንጀሮቻቸውንም ገደሉ፤ አሁንም ሞዓብ ሆይ! እንግዲህ ወደ ምርኮህ ሂድ” አሉ።
ከተሞቻቸውንም አፈረሱ፤ በመልካሞቹም እርሻዎቻቸው ሁሉ ላይ እስኪሞሉ ድረስ እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ድንጋይ ይጥል ነበር፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከተሞቻቸውንም ቅጥር አፈረሱ፤ የሚያምሩትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወንጭፎችም ከብበው መቱአቸው።