2 ነገሥት 3:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህ የጦር ደም ነው፤ እነዚያ ነገሥታት እርስ በርሳቸው ተጋደሉ፤ ባልንጀሮቻቸውንም ገደሉ፤ አሁንም ሞዓብ ሆይ! እንግዲህ ወደ ምርኮህ ሂድ” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ “ያ እኮ ደም ነው! ያለ ጥርጥር ነገሥታቱ እርስ በርስ ተዋግተው ተራርደዋል። እንግዲህ ሞዓብ ወደ ምርኮህ ዙር!” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ “ይህ ነገር ደም ነው! የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል! እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ!” ተባባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ “ይህ ነገር ደም ነው! የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል! እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ!” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርግጥ ነገሥታት እርስ በርሳቸው ተዋጉ፤ እርስ በርሳቸውም ተጋደሉ፤ ሞዓብ ሆይ! እንግዲህ ወደ ምርኮህ ሂድ፤” አሉ። |
ወደ እስራኤልም ሰፈር በመጡ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው ሞዓባውያንን መቱ፤ እነርሱም ከፊታቸው ሸሹ፤ ሞዓባውያንንም እየመቱ ወደ ሀገሩ ውስጥ ገቡ።
እግዚአብሔርም ለሶርያውያን የሰረገላ ድምፅ፥ የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቶአቸዋልና፥ እርስ በርሳቸው “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ይከቡን ዘንድ የኬጤዎናውያንንና የግብፃውያንን ነገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ይባባሉ ነበር።
ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረኩትም፤ ምርኮውም ብዙ ነበርና ምርኮውን እየሰበሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።
ጠላትም፦ ‘አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ነፍሴንም አጠግባታለሁ፤ በሰይፌም እገድላለሁ፤ በእጄም እገዛለሁ’ አለ።
የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ። በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፤ እንደ ተተወ እንቍላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም።
ምርኮውን ሲካፈል፥ በኀያላኑም ቸብቸቦ ላይ ወዳጆችን ሲወዳጅ ያገኙት አይደለምን? የሲሣራ ምርኮ በየኅብሩ ነበረ፤ የኅብሩም ቀለም የተለያየ ነበረ፤ የማረከውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአንገቱ ላይ ነበረ።