La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 3:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ሁሉ እነ​ዚያ ነገ​ሥ​ታት ሊወ​ጉ​አ​ቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ፥ “ሁላ​ችሁ መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ይዛ​ችሁ ርዱን” ብለው በሀ​ገ​ራ​ቸው ሁሉ ጮኹ። ተሰ​በ​ሰ​ቡም፤ ወጥ​ተ​ውም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ቆሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ነገሥታቱ ሊወጓቸው መምጣታቸውን ሞዓባውያን ሁሉ ሰምተው ነበርና፣ ልጅም ሆነ ሽማግሌ፣ መሣሪያ መያዝ የቻለ ሁሉ ተጠርቶ በመውጣት በጠረፉ ላይ ይጠባበቅ ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሞዓባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፥ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው በመውጣት በጠረፉ ላይ ተጠባበቁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሞአባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፥ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው በመውጣት በጠረፉ ላይ ተጠባበቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሞዓባውያንም ሁሉ ነገሥታት ሊወጉአቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ በወገባቸው ሰይፍ የሚታጠቁ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም በአገሩ ድንበር ላይ ቆሙ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 3:21
4 Referencias Cruzadas  

በከ​ተ​ማ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት የከ​ተ​ማው ሰዎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ችም ኤል​ዛ​ቤል እን​ዳ​ዘ​ዘ​ቻ​ቸ​ውና ወደ እነ​ርሱ በተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እንደ ተጻ​ፈው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


በነ​ጋ​ውም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ጊዜ፥ እነሆ፥ ውኃ በኤ​ዶ​ም​ያስ መን​ገድ መጣ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውኃ ሞላች።


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ፀሐ​ይም በው​ኃው ላይ አን​ጸ​ባ​ረቀ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም በፊ​ታ​ቸው ውኃው እንደ ደም ቀልቶ አዩና፦


እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ።