2 ነገሥት 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞላል፤ እናንተም፥ ከብቶቻችሁም፥ እንስሶቻችሁም፥ ትጠጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ሸለቆው ግን በውሃ ይሞላል፤ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና ሌሎች እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም፥ ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፤ እናንተ፥ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ነፋስ አታዩም፤ ዝናብም አታዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውሃ ይሞላል፤ እናንተም ከብቶቻችሁም እንስሶቻችሁም ትጠጣላችሁ።’ |
እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ።
በምድረ በዳም በተጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓለቱ ውስጥ ያፈልቅላቸው ነበር፤ ዓለቱም ተሰነጠቀ፤ ውኃውም ይፈስስላቸው ነበር፤ ሕዝቤም ይጠጡ ነበር።