ስላልወሰዳቸው ዓምዶች፥ ስለ ባሕሩም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦
2 ነገሥት 25:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የናስም ጕልላት ነበረበት፤ የጕልላቱም ርዝመት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው የናስ መርበብና ሮማኖች ነበሩ፤ እንዲሁም ደግሞ በሁለተኛው ዓምድ ላይ መርበብ ነበረበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ዐምድ ከፍታው ዐሥራ ስምንት ክንድ ሲሆን፣ የናስ ጕልላት ነበረው፤ የጕልላቱ ርዝመት ሦስት ክንድ ሆኖ፣ ዙሪያውን በሙሉ የናስ መርበብና የሮማን ፍሬዎች ቅርጽ ነበረው፤ ሌላውም ዐምድ ከነቅርጾቹ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ ዐምድ ስምንት ሜትር ነበረው፤ ጉልላቱ ከነሐስ የተሠራ ነበር፤ የጉልላቱም ቁመት አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ በዙሪያውም ከነሐስ በተሠራ መረብ ላይ የሮማን ፍሬ ቅርጽ የመሰለ ፈርጠኛ ጌጥ ተሠርቶበት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ዐምድ ስምንት ሜትር ነበረው፤ ጉልላቱ ከነሐስ የተሠራ ነበር፤ የጉልላቱም ቁመት አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ በዙሪያውም ከነሐስ በተሠራ መረብ ላይ የሮማን ፍሬ ቅርጽ የመሰለ ፈርጠኛ ጌጥ ተሠርቶበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአንዱም ዐምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፤ የናስም ጕልላት ነበረበት፤ የጕልላቱም ርዝመት ሦስት ክንድ ነበረ፤ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው የናስ መርበብና ሮማኖች ነበሩ፤ እንዲሁም ደግሞ በሁለተኛው ዐምድ ላይ መርበብ ነበረበት። |
ስላልወሰዳቸው ዓምዶች፥ ስለ ባሕሩም፥ ስለ መቀመጫዎቹም፥ በዚች ከተማ ስለ ቀሩት ዕቃዎች ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦