La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 23:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​ስ​ያ​ስም ዘወር ብሎ በከ​ተ​ማው የነ​በ​ሩ​ትን መቃ​ብ​ሮች አየ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በበ​ዓል ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ ልኮ ከመ​ቃ​ብ​ሮቹ አጥ​ን​ቶ​ቹን አስ​ወጣ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይም አቃ​ጠ​ላ​ቸው፥ አረ​ከ​ሰ​ውም። ዘወ​ርም ብሎ ይህን ቃል ወደ ተና​ገ​ረው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መቃ​ብር ዐይ​ኖ​ቹን አቀና። እን​ዲ​ህም አለ፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮስያስ ዘወር ሲል በኰረብታው ላይ የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ዐፅሞቹንም ከየመቃብሩ አስወጣ፤ ያ የእግዚአብሔር ሰው አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ መሠዊያውን ለማርከስ ሲል ዐፅሞቹን በላዩ ላይ አቃጠለበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፥ በኰረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮችን አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን ዐፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፤ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህን ትንቢት ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር አይቶ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮስያስም ዘወር ብሎ በተራራው የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ኢዮርብዓምም በበዓል ጊዜ በመሠዊያ አጠገብ ሲቆም እነዚህን ነገሮች የተነበየ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ልኮ፥ ከመቃብሮቹ አጥንቶቹን አስወጣ፤ በመሠዊያውም ላይ አቃጠላቸው፤ አረከሰውም። ዘወርም ብሎ ወደ ተናገረው ወደ እግዚአብሔር ሰው መቃብር ዐይኖቹን አቅንቶ

Ver Capítulo



2 ነገሥት 23:16
6 Referencias Cruzadas  

በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ውስጥ ባሉት በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የተ​ና​ገ​ረው ነገር በእ​ው​ነት ይደ​ር​ሳ​ልና።”


ሐው​ል​ቶ​ቹ​ንም ሁሉ አደ​ቀቀ፥ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ሁሉ ቈረጠ፤ በስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም የሙ​ታ​ንን አጥ​ንት ሞላ​በት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሬሳ​ዎች በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት አኖ​ራ​ለሁ፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ዙሪያ እበ​ት​ና​ለሁ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የመ​ጣ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን አማ​ል​ክት ካላ​ቸው፥ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይታ​በል ዘንድ አይ​ቻ​ልም።