እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
2 ነገሥት 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንዲህ ሲል ተናገረ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት እጅ እንዲህ ሲል ተናገረ |
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእርሱ በፊት የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵሰት አድርጎአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና፥
ነገር ግን አልሰሙም፤ እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ክፉ ይሠሩ ዘንድ ምናሴ አሳታቸው።
የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በነቢያቱ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፤ አላደመጡም፤ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።