አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ። ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጕልበቱ መካከል አቀርቅሮ በግንባሩ ወደ ምድር ተደፋ።
2 ነገሥት 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ። |
አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ። ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጕልበቱ መካከል አቀርቅሮ በግንባሩ ወደ ምድር ተደፋ።
ንጉሡም ይጠሩት ዘንድ የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እርሱም ሄዱ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ አገኙት። የአምሳ አለቃውም፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠራሃል ፈጥነህ ና፤ ውረድ” አለው።
ኢዮሣፍጥም፥ “በእርሱ እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን?” አለ። ከእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮች አንዱ፥ “ኤልያስን እጁን ያስታጥብ የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ” ብሎ መለሰ።
እንዲሁም ሄደች፤ ወደ እግዚአብሔርም ሰው ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ያችን ሴት ወደ እርሱ ስትመጣ ባያት ጊዜ ሎሌውን ግያዝን፥ “እነኋት፥ ሱማናዊት መጣች፤