2 ነገሥት 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪያፍራቸውም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ፥ “ላኩ” አለ፤ አምሳም ሰዎች ላኩ፤ ሦስት ቀንም ፈልገው አላገኙትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሆንም ለማለት ዕፍረት እስኪሰማው ድረስ ግድ አሉት፤ ስለዚህ፣ “በሉ እንግዲያው ላኳቸው” አለ። እነርሱም ዐምሳ ሰዎች ላኩ፤ ሰዎቹም ሦስት ቀን ሙሉ ፈልገው ሳያገኙት ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን እምቢ ለማለት እስኪያሳፍረው ድረስ አጥብቀው ስለ ለመኑት በጉዳዩ ተስማማና ኀምሳ ሰዎች ሄደው ሦስት ቀን ሙሉ ኤልያስን ፈለጉት፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን እምቢ ለማለት እስኪያሳፍረው ድረስ አጥብቀው ስለ ለምኑት በጉዳዩ ተስማማና ኀምሳ ሰዎች ሄደው ሦስት ቀን ሙሉ ኤልያስን ፈለጉት፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪያፍርም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ “ስደዱ” አለ፤ አምሳም ሰዎች ሰደዱ፤ ሦስት ቀንም ፈልገው አላገኙትም። |
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም፤ ሳይወሰድም እግዚአብሔርን ደስ እንደ አሰኘው ተመስክሮለታል።