2 ነገሥት 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም ጸሓፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ንጉሡም ላኩበት፤ ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ፣ ታሪክ መዝጋቢውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኀላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ። |
የኬልቅዩም ልጅ ኤልያቄም ሳምናስም ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና በሱርስት ቋንቋ ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በዕብራይስጥም ቋንቋ አትናገረን፤ በቅጥርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ ለምን ትናገራለህ?” አሉት።
የቤቱ አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሓፊው ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ ገቡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
በነገሠም በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ምድሪቱንና የእግዚአብሔርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የሴልያ ልጅ ሳፋን፥ የከተማዪቱም አለቃ መዕሴያ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የኢዮአካዝ ልጅ ኢዮአክ የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ ዘንድ ሰደዳቸው።
እነሆ እናንተ ቀድሞ ትፈሩአቸው የነበሩ በግርማችሁ ይፈሩአችኋል፤ ከእናንተም የተነሣ ይንቀጠቀጣሉ። መልእክተኞች መራራ ልቅሶን እያለቀሱ ይላካሉ፤ ሰላምንም ይለምናሉ።
የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፥ የሠራዊቱ ጸሓፊ ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን፥ ጸሓፊውንም ሳምናስን፥ የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።