2 ነገሥት 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። |
የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
አካዝም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረከት አድርጎ ሰደደው።
በዚያን ጊዜም ሕዝቅያስ ከእግዚአብሔር መቅደስ ደጆችና የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከለበጣቸው መቃኖች ወርቁን ቈረጠ፤ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠው።
አሳም ከእግዚአብሔር ቤትና ከንጉሥ ቤት መዝገብ ብርና ወርቅ ወስዶ፦ በደማስቆ ወደ ተቀመጠው ወደ ሶርያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር ላከ። እንዲህም አለው፦
ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም፥ ወርቁንና ብሩን፥ ከርቤውንና ዕጣኑን፥ ዘይቱንም፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት ሁሉ፥ ልብሱንና ዕንቍውን ሁሉ፥ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።