La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 15:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የጣ​ዖ​ታ​ቱን ቤት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። እር​ሱም የላ​ይ​ኛ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በር ሠራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ በየኰረብታው ላይ ያሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ገና አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በዚያ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር። ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን በኮረብቶች ላይ ያሉት መስገጃዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶች ላይ ባሉት መስገጃዎች ይሠዋና ያጥን ነበር። እርሱም የላይኛውን የእግዚአብሔርን ቤት በር ሠራ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 15:35
7 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ በነ​በ​ሩት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


በኮ​ረ​ብ​ታም ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አስ​ወ​ገደ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ሰባ​በረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ነቃ​ቀለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስ​ከ​ዚህ ዘመን ድረስ ያጥ​ኑ​ለት ነበ​ርና ሙሴ የሠ​ራ​ውን የና​ሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙ​ንም “ነሑ​ስ​ታን” ብሎ ጠራው።


የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም፥ ከበ​ር​ቴ​ዎ​ች​ንም፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም አለ​ቆች፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ረ​ዱት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በው​ስ​ጠ​ኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ ንጉ​ሡ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።


በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ዕጠኑ፤ እያለ የይ​ሁ​ዳን ሕዝ​ብና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች አዝዞ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያፈ​ረሰ ይህ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?