“የምሥራቁንም መስኮት ክፈት” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም፥ “ወርውር” አለው፤ ወረወረውም እርሱም፥ “የእግዚአብሔር መድኀኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶርያ የመዳን ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸውም ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ” አለ።
2 ነገሥት 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም ደግሞ፥ “ፍላጻዎችህን ውሰድ” አለው ወሰዳቸውም። የእስራኤልንም ንጉሥ፥ “ምድሩን ምታው” አለው። ንጉሡም ሦስት ጊዜ መትቶ ቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “በል ቀስቶቹን ውሰድ” አለው፤ የእስራኤልም ንጉሥ ወሰደ። ኤልሳዕም፣ “መሬቱን ውጋ” አለው፤ እርሱም ሦስት ጊዜ ወግቶ አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን “ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ!” አለው። ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን “ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ!” አለው። ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም “ፍላጻዎቹን ውሰድ፤” አለው፤ ወሰዳቸውም። የእስራኤልንም ንጉሥ “ምድሩን ምታው፤” አለው። ሦስት ጊዜም መትቶ ቆመ። |
“የምሥራቁንም መስኮት ክፈት” አለ፤ ከፈተውም። ኤልሳዕም፥ “ወርውር” አለው፤ ወረወረውም እርሱም፥ “የእግዚአብሔር መድኀኒት ፍላጻ ነው፤ ከሶርያ የመዳን ፍላጻ ነው፤ እስክታጠፋቸውም ድረስ ሶርያውያንን በአፌቅ ትመታለህ” አለ።
የእግዚአብሔርም ሰው አዝኖ፥ “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መትተኸው ቢሆን ኖሮ ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በመታኻቸው ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ሶርያን ትመታለህ” አለ።
አዛሄልም ከአባቱ ከኢዮአካዝ እጅ በሰልፍ የወሰዳቸውን ከተሞች የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ መልሶ ከአዛሄል ልጅ ከወልደ አዴር እጅ ወሰደ። ዮአስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእስራኤልንም ከተሞች መለሰ።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም በአወረደ ጊዜ ዐማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።