ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳቢያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች።
2 ነገሥት 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረ ዘመን ሁሉ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ዮዳሄ ያስተምረው በነበረበት ዘመን ሁሉ፣ ኢዮአስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ዮዳሄ ይመክረውና ያስተምረው ስለ ነበር፥ ኢዮአስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ዮዳሄ ይመክረውና ያስተምረው ስለ ነበር፥ ኢዮአስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢዩ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ መንገሥ ጀመረ፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳብያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች። |
ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳቢያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች።
ነገር ግን በኮረብቶቹ ላይ ያሉ የጣዖት መስገጃዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም ገና በኮረብቶቹ ላይ ባሉት የጣዖት መስገጃዎች ይሠዋና ያጥን ነበር።
ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ኢዮአስ እንዳደረገ ሁሉ እንጂ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላደረገም።