2 ነገሥት 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሣጥኑም ውስጥ ብዙ ገንዘብ መኖሩን በሚያዩበት ጊዜ ሁሉ፣ የንጉሡ ጸሓፊና ሊቀ ካህናቱ መጥተው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባውን ገንዘብ ቈጥረው በየከረጢቱ በማስገባት ቋጥረው ያኖሩት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቁጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቊጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑ ዮዳሄ ግን ሣጥን ወስዶ መክደኛውን ነደለው፤ በመሠዊያውም አጠገብ ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚገቡበት መግቢያ በስተ ቀኝ አኖረው፤ ደጁንም የሚጠብቁ ካህናት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ ሁሉ ያኖሩበት ነበር። |
የተሰበሰበውንም ገንዘብ ሥራውን በሚሠሩና የእግዚአብሔርን ቤት በሚጠብቁት እጅ ይሰጡ ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ ግንበኞችና አናጢዎች ይሰጡ ነበር።
የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
ንጉሡም ካህኑን ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክዩንም ልጅ ዓክቦርን፥ ጸሓፊውንም ሳፋንን፥ የንጉሡንም ብላቴና ዓስያን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦
ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናት በረኞቹንም፥ ለበዓልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠሉት፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰዱት።
ንዕማንም፥ “ሁለት የብር መክሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለቱንም መክሊት ብር ተቀብሎ በሁለት ከረጢት ውስጥ ጨመረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ።
የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር።
ሣጥኑም በሌዋውያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹሞች በደረሰ ጊዜ፥ ብዙ ገንዘብም እንዳለበት ባዩ ጊዜ፥ የንጉሡ ጸሓፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም እየመጡ ብሩን ከሣጥን ያወጡ ነበር፤ ሣጥኑንም ደግሞ ወደ ስፍራው ይመልሱት ነበር። እንዲሁም በየቀኑ ያደርጉ ነበር፤ ብዙም ገንዘብ ሰበሰቡ።
ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ብር ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ በባሕር ወደ ኢዮጴ ያመጡ ዘንድ ለሲዶናና ለጢሮስ ሰዎች መብልና መጠጥ፥ ዘይትም ሰጡ።