የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት ኢዮሳቡሄም የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱንም ወደ እልፍኝ ወሰደች፤ ከጎቶልያም ሸሸገችው፤ አልገደሉትምም።
2 ነገሥት 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ቤት ስድስት ዓመት ሸሸገችው። ጎቶልያም በሀገሩ ላይ ነገሠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ጎቶልያ ምድሪቱን በምትገዛበት ጊዜ ከሞግዚቱ ጋራ በእግዚአብሔር ቤት ተደብቆ ስድስት ዓመት ኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐታልያ በነገሠችበትም ስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ፥ ይሆሼባዕ ሕፃኑን ኢዮአስን በቤተ መቅደስ በመንከባከብ አሳደገችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐታልያ በነገሠችበትም ስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ፥ ይሆሼባዕ ሕፃኑን ኢዮአስን በቤተ መቅደስ በመንከባከብ አሳደገችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርስዋም ዘንድ ተሸሸጎ በእግዚአብሔር ቤት ስድስት ዓመት ያህል ተቀመጠ። ጎቶልያም በምድር ላይ ነገሠች። |
የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት ኢዮሳቡሄም የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱንም ወደ እልፍኝ ወሰደች፤ ከጎቶልያም ሸሸገችው፤ አልገደሉትምም።
በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮራውያንና በዘበኞች ላይ ያሉትን የመቶ አለቆች ወሰደ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አገባቸው፤ ከእነርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አማላቸው፤ የንጉሡንም ልጅ አሳያቸው።
ወደ አባቱም ቤት ወደ ኤፍራታ ገባ፤ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ።