ከእስራኤልም ልጆች ውስጥ የኢያኤል ልጅ ኢኮንያስ ዕዝራን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ልዩ ከሚሆኑ ከምድር አሕዛብ ወገን ሚስት ያገባን እኛ እግዚአብሔርን በድለናል፤ አሁንም ይህ ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አለ።