ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
2 ቆሮንቶስ 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው በቅድሚያ የተናገራችኋትን በረከታችሁን እንዲያዘጋጁ ወንድሞችን ማለድሁ፤ እንደዚህም የተዘጋጀ ይሁን፤ በረከትን እንደምታገኙበት እንጂ በንጥቂያ እንደ ተወሰደባችሁ አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡና ከዚህ በፊት ለመስጠት ቃል የገባችሁትን ስጦታ አጠናቅቃችሁ እንድትጠብቋቸው፣ እነርሱን መለመን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቻለሁ፤ እንግዲህ በልግስና ለመስጠት ያሰባችሁት ነገር በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት የተዘጋጀ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ልትሰጡ ቃል የገባችሁበትን የልግሥና ስጦታችሁ በቅድሚያ እንድታዘጋጁ እንዲያስታውሱአችሁ በማለት እነዚህ ወንድሞች ከእኔ ቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በምመጣበት ጊዜ የልግሥና ስጦታችሁ ዝግጁ ይሆናል፤ እናንተም የምትሰጡት በግድ ሳይሆን በፈቃደኛነት መሆኑን ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንደ በረከት ሆኖ ከስስት የማይሆን ይህ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን በረከት አስቀድመው እንዲፈጽሙ ወንድሞችን እለምን ዘንድ እንዲያስፈልገኝ አሰብሁ። |
ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም።
እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ ኤልሳዕ ተመለሰ፤ ወደ እርሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእስራኤል ነው እንጂ በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ ዐወቅሁ፤ አሁንም ከአገልጋይህ በረከት ተቀበል” አለው።
እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ።
በዚህም ያመሰገንናችሁ ምስጋና በእነርሱ ዘንድ ሐሰት እንዳይሆንብን፥ እንደ ነገርናቸውም ተዘጋጅታችሁ እንዲያገኙአችሁ ወንድሞችን ወደ እናንተ ላክናቸው።
ዓስካም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድደኸኛልና ውኃ የማጣቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ” አለችው። ካሌብም በልብዋ እንደ ተመኘችው የመከራዋንና የኀዘኗን ዋጋ ሰጣት።
ዳዊትም ወደ ሴቄላቅ በመጣ ጊዜ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ፥ “እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ” ብሎ ከምርኮው ላከላቸው።