La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኑሮ​አ​ችሁ በሁሉ የተ​ካ​ከለ ይሆን ዘንድ፥ የእ​ና​ንተ ትርፍ የእ​ነ​ር​ሱን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና፥ የእ​ነ​ር​ሱም ትርፍ የእ​ና​ን​ተን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ያሟላል፤ የእነርሱም ደግሞ በተራው የእናንተን ጕድለት ያሟላል፤ በዚህም ያላችሁን እኩል ትካፈላላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ፥ በዚህም ያላችሁን እኩል እንዲሆን፥ የአሁኑ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ በምትቸገሩበት ጊዜ የእነርሱ ሀብት ለእናንተ ችግር እንዲውል አሁን የእናንተ ሀብት ለእነርሱ ችግር ይዋል፤ በዚህ ዐይነት በመካከላችሁ እኩልነት ይኖራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ፤ በትክክል እንዲሆን፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 8:14
3 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር።


በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም።


ይህቺ የዚህ ሥራ አገ​ል​ግ​ሎት ግዳጅ የም​ት​ፈ​ጽ​መው ለዚህ ለቅ​ዱ​ሳን ችግር መሟ​ላት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቅ​ዱ​ሳን ዘን​ድም ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ታበ​ዛ​ለች።