2 ቆሮንቶስ 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ተጽናንተናል፤ በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፤ በሁላችሁ ዘንድ ሰውነቱን አሳርፋችኋታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም የተጽናናነው በዚህ ምክንያት ነው። ከእኛም መጽናናት በተጨማሪ በቲቶ ደስታ እኛም ይበልጥ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ሁላችሁም መንፈሱን አሳርፋችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ተጽናንተናል፤ ክመጽናናታችንም ሌላ ስለ ቲቶ ደስታ እጅግ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ልቡ በሁላችሁም እረፍት አግኝቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጽናናታችንም በላይ ቲቶ ባገኘው ደስታ ይበልጥ ተደስተናል፤ የተደሰትነውም ሁላችሁም ቲቶን ስላጽናናችሁትና መንፈሱንም ስላሳረፋችሁት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፥ መንፈሱ በሁላችሁ ዐርፎአልና፤ |
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ።
ስለ እናንተ ለእርሱ በተመካሁበት ሁሉ አላሳፈራችሁኝምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትምክህታችን እውነት ሆነ።
ስለዚህም እጅግ ያመሰግናችኋል፤ እንደ ታዘዛችሁለት፥ በመፍራትና በመደንገጥም እንደ ተቀበላችሁት ያስባችኋል።