አንተን ግን ከጠላትህ አፍ አድኖሃል፥ በበታችህም ጥልቅ ባሕር፥ ፈሳሽ ምንጭም አለ፥ ማዕድህም በስብ ተሞልታ ትወርዳለች።
2 ቆሮንቶስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ የደረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእኛም በእናንተ ላይ የደረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በልባችሁ አዝናችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኛ አልተገደባችሁም፤ ነገር ግን በውስጣችሁ ተገድባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ፍቅራችንን አልቆጠብንባችሁም፥ እናንተ ግን ቆጥባችሁብናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ፍቅራችሁን ነፈጋችሁን እንጂ እኛስ አልነፈግናችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኛ አልጠበባችሁም በሆዳችሁ ግን ጠቦባችኋል፤ |
አንተን ግን ከጠላትህ አፍ አድኖሃል፥ በበታችህም ጥልቅ ባሕር፥ ፈሳሽ ምንጭም አለ፥ ማዕድህም በስብ ተሞልታ ትወርዳለች።
የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ታገሡን፥ የበደልነው የለም፤ የገፋነውም የለም፤ ያጠፋነውም የለም፤ የቀማነውም የለም።
ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?