2 ቆሮንቶስ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያ የሚያልፈው ክብር ካገኘ፥ ያ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት እጅግ ክብር ያገኝ ይሆን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያልፈው ያን ያህል ክብር ከነበረው፣ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ ይሻር የነበረው በክብር ከደረሰ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት ልቆ እጅግ አይከብርም! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ እየደበዘዘ ይሄድ የነበረው ነገር ይህን ያኽል ክብር ከነበረው፥ ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረው ነገርማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና። |